ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙሃንና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙሃንና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ነው።

የውይይቱ ዓላማ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ቀደም ሲል በተካሄዱ ምርጫዎች በመገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ ሲያቀርቡ ያጋጠማቸውን ችግሮች በማንሳት ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊና ሚዛናዊ አሰራር ለመዘርጋት ነው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ረቂቅ መመሪያው ለመድረኩ ተሳታፊዎች ቀርቦ አስተያየት የሚሰበሰብ ይሆናል።

ምርጫ ቦርድ በሚያወጣው መመሪያና በሚወስነው የድልድል መስፈርት መሰረት ድልድሉ በሶፍትዌር በመታገዝ እንደሚከፋፈልም ተገልጿል።

በዛሬው መድረክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓት ላይ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሏል።

ህዳር 11, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share