በ2013 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ሀገራ የሚላኩ ምርቶች መጠን 18 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የምክር ቤቱ አባላት ላነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም በበጀት ዓመቱ የኮሮና ቫይረስ፣ የአንበጣ መንንጋ እና የጎርፍ አደጋ መከሰት በኢኮኖሚው ላይ ጫና ማሳደሩን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ዜጎች ከመኖሪያ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጉን እና በተለያ ምክንያት የተሻገሩ በርካታ ፕሮጀክቶች መኖራቸው ኢኮኖሚው ላይ ተጽእኖ ማሳደራቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በእነዚህ እና በተለያዩ ፈተናዎች ላይም ሆና ኢትዮጵያ በእድገት ጎዳና ላይ መሆኗን ነው ያወሱት፡፡፡

ከለውጥ በኋላ 2011 ዓ.ም 9 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላም 6 ነጥብ 1 በመቶ እድገት መመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

የወጪ ንግድ በተያዘው በጀት ዓመት 18 በመቶ መጨመሩን በመግለጽ በዚህም 3 ነጥበ 5 ቢሊየን ዶላር ማግኘት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

የውጭ ኢንቨስትመንት 20 በመቶ ማደጉን በመጥቀስም ክልሎች መሬት በማቅረብ ረገድ ያሳዩት ተነሳሽነት የሚበረታ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በበጀት ዓመቱ ካለፈው ዓመት አንጻር 20 በመቶ ተጨማሪ ብድር ተሰጥቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዚህ ውስጥም ከ74 በመቶ በላዩ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የብድር ምልሰት ምጣኔ ለባንኮች ከፍተኛ ተግዳሮት መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ችግሩን ለመቅረፍ ባንኮች አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ለሚስተዋለው የዋጋ ንረት ዋነኛዎቹ መንስኤዎች አቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣም እንዲሁም በንግድ ሰንሰለቱ አላስፈላጊ የህገ ወጥ ደላሎች ጣልቃ ገብነት መኖር መሆናኑንም አንስተዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

ሰኔ 28, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share