በፌደራል መንግስት እና በህውሀት መካከል የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር ሊኖር እንደማይገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ

በፌደራል መንግስት እና በህውሀት መካከል የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር ሊኖር እንደማይገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስቀመጠው የፌዴራል መንግስቱ ለድርድር ይቀመጥ ማለት ለህወሓት ህጋዊ እና ሞራላዊ የእኩልነት ደረጃ እንደመስጠት ተደርጎ ይቆጠራል።
አሁን ላይ ሁለቱ አካት ሊደራደሩ የሚችሉበት ህጋዊም ሞራላዊም አግባብ ካለመኖሩም በላይ የፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ እየሰራ ይገኛል።
ምክር ቤቱ አክሎም ፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ የሆነ ስልጣኑን ተጠቅሞ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ ካልቻለ እና መደራደርን ከመረጠ ወደ ፊት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ይገጥመዋል ብሏል፡፡
ይህም ማለት ደግሞ ሌሎች የፌዴሬሽኑ አካል የሆኑ የክልል መንግስታት የፌዴራሉን መንግስት ያለ ማንም ከልካይነት መገዳደር እንዲችሉ መፍቀድ ማለት ነው ሲል የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡

ህዳር 7, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share