በገቢ ምርቶች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ እና የኢንስፔክሽን ፍተሻ ከኢትዮጵያ የጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ እንዳይገቡ ታገዱ፡፡

በተደረገ የላብራቶሪ እና የኢንስፔክሽን ፍተሻ 3 ነጥብ 5 ሜ.ቶ ኤል ኢ.ዲ አምፖል፣ 25 ነጥብ 8 የኤሌክትሪክ ማከፋፋያ፣ 368 ካርቶን (368 ሺህ 800 ፍሬ) መጠን ያለው የሀይል አባካኝ አንፖል፣ 4 ሺህ 800 ፍሬ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ 8 ነጥብ 131 ሜ.ቶን የአርማታ ብረት፣ 12 ነጥብ 6 ሜ.ቶ ጥቅል ቆርቆሮ፣ 5 ሺህ ፍሬ የፍሎረሰንት አምፖል እንዳይገባ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም 293 ካርቶን የኤሌክትሪክ ሶኬት ማከፋፋያ፣ 55 ነጥብ 3 ሜ.ቶን የአተር ክክ፣ 24 ነጥብ 93ሜ.ቶ ሩዝ፣ 693 ነጥብ 8 ቶን ቀይ ሽንኩርት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡና የህብረተሰቡን ጤና፣ ደህንነትና ጥቅም እንዳይጎዱ መደረጉን የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ እያሱ ስምዖን መናገራቸዉን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡(ኤፍ ቢሲ)

ጥር 20, 2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share