በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ማዕከሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ 30 የዳያሊሲስ ማሽኖች እንደሚኖሩት ተጠቅሷል፡፡
የህፃናት ማቆያ ክፍል፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የቀዶጥገና ክፍል፣ የሀኪሞች ክፍል፣ የታማሚዎች ክፍል፣ለይቶ ማቆያ ክፍል እንዲሁም ሀኪሞች ታካሚዎቻቸውን በቅርበት የሚከታተሉበት ስፍራም ያለው መሆኑም ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ለ30 ታካሚዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለውና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው ይህ ማዕከል አሁን ላይ የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቀጣይም ማሽኖቹ ተገጥመው ወደሙሉ አገልግሎት ሲገባ ለኩላሊት ታካሚዎች ከፍተኛ እፎይታን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

ጥር 20, 2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share