በዚህ የተቀናበረ ድራማ ሕዝቡ ሳይታለል እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

‹የኤርትራ ጦር እያጠቃኝ ነው› የሚል ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ትህነግ የጦር ዩኒፎርሞችን አመሳስሎ በማምረትና የራሱን ወታደሮች በማልበስ ህዝብ ለማሳሳት እየሞከረ እንደሆነ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ “ሁመራና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል” ሲሉ የአገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ተናግረዋል፡፡

ሰራዊቱ በአሁኑ ወቅት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

የህወሃት ጁንታ በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ እንደወረረች በመግለጽ ሕዝብን እያደናገረ እንደሆነም አስታውቀዋል።

በዚህ የተቀናበረ ድራማ ሕዝቡ ሳይታለል ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ህዳር 3, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share