ከተለያዮ የህብረት ስራ ማህበራት ከአራቱም አቅጣጫ ተገኝተው ያደመቁት ትርዒቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት መነሻውን አድርጎ በተለያዮ የከተማዋ አካባቢዎች ተካሂዷል።
በተጨማሪም ከየካቲት 3 እስከ 7 በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደው የህብረት ስራ ኤግዚቢሽን እና ባዛር በይፋ የተከፈተ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመውበታል።
የኢግዚቢሽኑን በይፋ መከፈት ያበሰሩት የፊዴራል ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽነር ዋና አማካሪ አቶ ዳሪቦ ሁሴን ሁሉም የህብረተሰብ አካላት በኤግዚቢሽኑ ላይ በመሳተፍ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ጋብዘዋል።