በዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው 9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚብሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሺን ማእከል በይፋ ተከፈተ።wafaadmin | Posted on February 10, 2022 | በዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው 9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚብሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሺን ማእከል በይፋ ተከፈተ።ኤግዚቢሽኑን አቶ ዳሪቦ ሁሴን የፌዴራል ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽነር ዋና አማካሪ እንዲሁም አቶ አደም ኑሪ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሀላፊ በይፋ ከፍተውታል።የህበረት ስራ ማህበራት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የበኩላቸውን ያበረክቱ ዘንድ ሁሉም አካላት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አቶ አደም ኤግዚቢሽኑን በከፈቱበት ንግግራቸው አሳስበዋል።ሀላፊው አክለውም ሀገራችን ተገዳ በገባችበት ጦርነት ሳቢያ ኪሳራ የገጠማቸውን በተለያዮ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት በጋራ ትብብር ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንዲመለሁ ማገዝ ከሁሉም ማህበራት የሚጠበቅ ነው ብለዋል።9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚብሽንና ባዛር ከዛሬ የካቲት 3 እስከ የካቲት 7 2014 ለሸማቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል። የካቲት 3, 2014 ዓ.ም Please follow and like us: Post Navigation ← Previous PostNext Post →