በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ ወደ ኬንያ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ የሚመራ ልዑክ ከኬኒያው አቻው ጋር በሁለትዮሽና በቀጠናው ሠላም ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን ወደ ኬንያ አቅንቷል።

የተቋሙ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ልዑኩ በናይሮቢ በሚኖረው የአራት ቀናት ቆይታ ከኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በሁለትዮሽና በቀጠናው ሠላም ዙሪያ ውይይቶች እና የልምድ ልውውጦች ያደርጋል

በተለይም ልዑኩ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የኬንያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን በመቆሙ ላሳዩት አቋም ምስጋናም እንደሚቀርብም አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እንደሚደረግና በኬንያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሀገር ውጭ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛውን ቅርንጫፍ ለማቋቋም እንደሚመክር ነው ዋናዉ ጸሐፊው የገለጹት። (ኤፍ )

ሐምሌ 10, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share