በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍልዉሃ አካባቢ ተነስቶ የነበረዉን እሳት አደጋ መቆጣጠሩን የእሳት እና አደጋ ስጋት ኮሚሽን አስታወቀ

የእሳት እና አደጋ ስጋት ኮሚሽን የእሳት እና ድንገተኛ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ወንደምአገኝ አልታየ እንደተናገሩት ከሆነ አደጋዉ የተከሰትዉ ልዩ ቦታዉ ፍልዉሃ አደባባይ ወደ አምባሳደር የሚወስደዉ መንገድ ላይ የሚገኙ ሬስቶራንቶች እና ሌሎች ንግድ ቦታዎች ላይ ሲሆን በአጭር ሰአትም ልንቆጣጠረዉ ችለናል ብለዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘዉም ባደረግነዉ ፈጣን ምላሽ ብዙ ንብረትን ማዳን ችለናለ ብለዋል።
በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ገና በመጣራት ላይ ሲሆን የፖሊስ ፎረንሲክስ አባላት የእሳቱን መንሰኤ እያጣሩ ነዉ መባሉንም አዲስ ዘይቤ በተጨማሪ ዘግቧል፡፡

ህዳር 7, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share