በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ሀይል ፣ በሰሜን ወሎ ግንባር በተሰማራው የመከላከያ ሠራዊታችን ተመታ።

ዓርሚ ሁለት የሚባልና በከሀዲው ሜ/ጄ/ል ዮሀንስ በቅፀል ስሙ ጆን ፣ በምክትሉ ከሀዲው ማዕሾ በየነ እና ከሀዲው ከበደ ፍቃዱ እንዲሁም በሜካናይዝድ አዛዡ ከሀዲው ኮ/ል ገ/ስላሴ የተመራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሀይል ድባቅ ተመቷል።
በግንባሩ የተሰማሩ ሁለት ክፍለ ጦር አዛዦ እንደተናገሩት ፥መንግስት የተናጠል የተኩሥ አቁም እርምጃውን ካነሳ በሁዋላ ከበላይ በተሠጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጋሸናን ዋና ማዕከል በማድረግ ከዋድላ እሥከ ላሊበላ መስመር ላይ የነበረውን የአሸባሪውን ሀይል መደምሠሳቸውን አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰዓት ጠላት በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት ፣ ልዩ ሀይል እንዲሁም የሚሊሻ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደር ከበባ ውሥጥ ሆኖ ይገኛል።
ይህ የተዳከመ የጠላት ሀይል በጋሸና ፣ በመቄት ፣ በሙጃ ፣ በንፋሥ መውጫ አካባቢዎች እየተመታና እየተበተነ ይገኛል ብለዋል።
በነዚህ አካባቢዎች በጠላት ላይ በተደረገ ጥቃት 3 ድሽቃ ፣ 6 ሺ የድሽቃ ጥይት ፣ 87 የዕጅ ቦንብ ፣ 229 ክላሽንኮቭ ነፍስ ወከፍ መሣሪያ ፣ 5ሺ የክላሽ ጥይት ፣ አንድ የጦርሜዳ መነፅር ሢማረክ ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የሠው ሀይል እና ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ 2 መድፎች እንዲሁም አንድ ዙ 23 መደምሠሥ መቻሉን ዋና አዛዦቹ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)

ነሐሴ 15, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share