በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል ሰብዓዊ እርዳታ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገለፀ፡፡

መንግስት ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ እንዲያቀርቡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት ከ40 የሚበልጡ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ከተማ የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ ጀምረዋል።

ተሽከርካሪዎቹ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎችን የጫኑ ሲሆን÷ የሰብዓዊ ዕርዳታው በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ለተጎዱ ወገኖች እንደሚሰራጭ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። (ኤፍ ቢ ሲ)

ሀምሌ 03, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share