በቦሌ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የህክምና ፍቃድ ሳይኖረው የኮቪድ -19 ህክምና ማዕከል በመክፈት አገልግሎት እየሰጠ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ የህክምና ፍቃድ ሳይኖረው ክሊኒክ በመክፈት የኮሮና ቫይረስ ህክምና ለተለያዩ ሰዎች ሲሰጥ ነው፡፡
የአየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከቦሌ ክፍለ ከተማ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ባለሙያዎች ጋር በሰሩት ጥናት ፥ፍቃድ ሳይኖረው ክሊኒክ በመክፈት የኮሮና ቫይረስ ህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ከተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ጳጉሜ 05,2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share