በቀጣይ የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላትን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲያከብር የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ

ሚኒስቴሩ በዓላቱን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን በሰጠው መግለጫ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው በዓላት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም በተለይም በአመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ፣ የገና እና የጥምቀት በዓላት አከባበር ላይ፥ ምዕመኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያከብር መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጉባኤው ወደቤተ እምነቶች የሚመጡ አማኞች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ እና የየቤተ እምነቱ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም ምዕመኑ በየትኛውም ሁኔታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና ንክኪን በመቀነስ እንዲሁም ንጽህናን በመጠበቅ የቫይረሱን ስርጭትና ያለውን ተጋላጭነት እንዲቀንስም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ተጨባጭ የጤና ችግር መሆኑን በመረዳት ለአፍታም ቢሆን መዘናጋት አይገባምም ማለቱን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ታህሳስ 16,2013 ዓ.ም

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share