ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎችን ለመመለስ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡
የዚሁ ዕቅድ አካል የሆነው የመጀመሪያው ዙር ተመላሾች ዛሬ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡
ተመላሾቹን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛሉ፡፡
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዛሬ ማለዳ በመጀመሪያው በረራ ከሪያድ 157 ህጻናትንና 341 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ላሉት ዜጎች በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ቦታም ተዘጋጅቷል።(ኤፍ ቢ ሲ)