በሩሲያ-ዩክሬን ቀውስ ላይ በመከረው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ወንበሯን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል የዲፕሎማሲ ውሳኔ የተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የሩሲያ – ዩክሬን ግጭትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ጉዳዩን ከሌላው የሚለየው ከግጭቱ ጀርባ ያሉ ሃይሎች ማንነት መሆኑን ጠቅሰው፥ ግጭት ውስጥ ያሉት አካላት ኒውክሌር የታጠቁ መሆናቸውን አንስተዋል።
በዚህ ጦርነት አሸናፊ የሚሆን የለም ያሉት ቃል አቀባዩ ሁለቱም አካላት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ኢትዮጵያ መጠየቋን አስታውሰዋል።
በሁለቱ ወገኖች ቀውስ ላይ በመከረው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ወንበሩን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏም በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል። (ኤፍ ቢ ሲ)

 

መጋቢት 1,2014 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share