ተሳታፊዎቹ በዚህ ጉባኤ በአፍሪካ የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ብለው እንደሚጠብቁ ለኢዜአ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት በጉባኤው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የወጣቶች ስራ ፈጠራን ማጠናከር ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ፥ ይህም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍታት ያስችላል ብለዋል።
ውሳኔዎቹ አፍሪካ የሚያጋጥሟትን ችግሮች ተሻግራ ድል እንድታደርግ የሚያስችሉ ናቸው።
በአፍሪካ በሴቶችና ህጻናት እንዲሁም በሌሎች ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት መስራት አለብን ፤ በዚህ ጉበኤም ሰላምና መረጋጋትን በአፍሪካ ለማስፈን የሚያስችሉ ውሳኔዎችን እንጠብቃለን ብለዋል።