በሀገር ውስጥና በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን አንድና ብዙ ሆነን እንነሣ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ‘‘ብዙ ሆነን፣ ብዙ ነገሮችን በብዙ መስኮች። በሀገር ውስጥና በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን፣ ሁላችንም ለኢትዮጵያ ከልብ ተነሥተን፣ የክረምቱን ግብርናና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ አረንጓዴ ዐሻራን፣ 2ኛው ዙር የሕዳሴ ግድብን ሙሌት፣ ሉዓላዊነታችንን ማስጠበቅን፣ ዲፕሎማሲያችንን፣ በአንድ ጊዜ፣ አንድና ብዙ ሆነን፣ በብዙ መስኮች ለማሳካት እንነሣ’’ ብለዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

ሰኔ 30፤2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share