ፕሮጀክቱ “ልማታዊ ሴፍቲኔት ለከተሞች ሁለንተናዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው በአገር አቀፍ ደረጃ ድሬዳዋ ላይ በይፋ የሚጀመረው።
በሚኒስቴሩ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መኮንን ያኢ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በተመረጡ 83 ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል።
ፕሮጀክቱ በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት 550 ሚሊየን ዶላር በጀት የሚተገበርና 816 ሺህ 500 ዜጎችን በቀጥታና በልማት ስራዎች በማሳተፍ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በስነ ስርአቱ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።(ኤፍ ቢ ሲ)