በሀገሪቷ ውስጥ የሚካሄዱ ሁነቶች ከፕሮቶኮል አንፃር ብዙ ሊሰራባቸው እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን የማኔጅመንት አባላት ጋር በተቋሙ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና በቀጣይ ሊተኮርባቸው በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ሁነቶች ወጪ ቆጣቢ፣ ደረጃቸውን የጠበቁና የታለመላቸውን ዓላማ የሚያሳኩ ሆነው ይዘጋጁ ዘንድ ወጥነት ያለውና ዓለም አቀፍ የሁነት ዝግጅት ፕሮቶኮሎችን የተከተለ አሰራር በመዘርጋትና አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት ረገድ ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ፕሬዚዳንቷ ገልፀዋል፡፡
የዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋንታዬ ጌታነህ በበኩላቸው ተቋሙ የሀገሪቱን መልካም ገፅታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እያደረገ ያለውን ጥረት ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን አስታውሰው የሀገሪቱን የሁነት ኢንዱስትሪ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ሐምሌ 19, 2013 ዓ.ም

Please follow and like us:
Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share