ሰልፎች

የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የከሀዲውን ትህነግን ሴራ በመቃዎም ሰልፍ ወጡ፡፡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ ሰልፉ በተካሄደበት የጅግጅጋ ስታድየም ባደረጉት ንግግር ስግብግቡ ጁንታ አፀያፊ ተግባር በሶማሌ ሕዝብ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያሳረፈው ቁስል ሳይሽር በቅርቡ የሃገር አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ተግባርም እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። በተያያዘም  ከሀዲው የትህነግ ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የወሰደውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀዋሳ ተካሂዷል። በሰላማዊ ሰልፉ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። ሰልፈኞቹ ከሃዲው የህወሃት ጁንታ ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚቃወሙ መፈክሮችን በመያዝ አውግዘዋል፡፡ በተመሳሳይ የጅማ እና አጋሮ ከተሞች ነዋሪዎች መንግስት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን የህግ ማስከበር ስራ እንደሚደግፉ ባካሄዱት ሰልፍ ገልጸዋል፡፡ (ዘገባው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ነው)

ህዳር 3, 2013 ዓ.ም.

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Follow by Email
YouTube
YouTube
LinkedIn
LinkedIn
Share