የኢንዱስትሪው ዘርፍ በአጠቃላይ ዓመታዊ ምርት ውስጥ ያለው ድርሻ 16 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል

 

የኢንዱስትሪው ዘርፍ በአጠቃላይ ዓመታዊ ምርት ውስጥ ያለው ድርሻ 16 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል

ነሐሴ30/2009

የኢንዱስትሪው ዘርፍ የዛሬ 10 ዓመት ከሀገሪቱ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርት ውስጥ ከነበረው የ10 በመቶ ድርሻ አሁን ወደ 16 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል።

በነዚህ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ዘርፍ በየዓመቱ የ20 በመቶ እድገት እያስመዘገበች ቢሆንም በአምራቹ ዘርፍ እንደተፈለገው ለውጥ አልመጣም ተብሏል።

የአምባሳደሮችና የሚሲዮን ሀላፊዎች ስብሰባ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

የአምባሳደሮችና የሚሲዮን ሀላፊዎች ስብሰባ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

ነሐሴ29/2009

የአምባሳደሮችና የሚሲዮን ሃላፊዎች ስብሰባ በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ስብሰባው “ተቋማዊ ለውጥ ለውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ስኬት” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ ኢትዮጵያን በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበርና ተደማጭነቷን ለማጉላት የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩና ለቀጣይ ስራዎች ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥረው ያለፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከቻይና የተለያዩ የኢንዱትሪ ማህበራት ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

 

/ ኃይለማርያም ከቻይና የተለያዩ የኢንዱትሪ ማህበራት ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

ነሐሴ27/2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቻይና ከተለያዩ የኢንዱትሪ ማህበራት የተወጣጣ ልዑካን ቡድን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፥ በኢትዮጵያና ቻይና መንግሥት መካከል የጠበቀ ወዳጅነት መኖሩን ለልኡካን ቡድኑ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባ ተጀመረ

 

የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባ ተጀመረ

ነሐሴ25/2009

የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች  ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ስብሰባው ሚኒስቴሩ በ2009  በጀት ዓመት ባከናወናቸው ስራዎች ላይ እንደሚያተኩር ተጠቀሟል።

በወጭ ንግድ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የዘርፍ መስሪያ ቤቶች ለተሳታፊዎች ገለጻ እንደሚሰጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

 

የኢፌዴሪ ምክትል / ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ነሐሴ25/2009

ኢትዮጵያ ድርቅን በመከላከልና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን በዘረጋቻቸው መዋቅሮች አጋር ድርጅቶች ቢጠቀሙ ውጤታማ ተግባር ማከናወን እንደሚችሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ሚስ ኡላ ፔደርሲንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper