አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከግብፅ የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ
ህዳር 19/03/2010
በግብፅ የኢፌዲሪ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከግብፅ ፓርላማ የአፍሪካ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ኤልሳይድ ፈሊፍል እና የኮሚቴው አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።