ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድና ደቡብ ኮሪያ ጋር ቢዝነስ ፎረሞችን አካሄደች

ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድና ደቡብ ኮሪያ ጋር ቢዝነስ ፎረሞችን አካሄደች

ህዳር 18/03/2010

ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድና ደቡብ ኮሪያ ጋር የቢዝነስ ፎረሞችን አካሂዳለች።

የቢዝነስ ፎረሞቹ በዛሬው እለት የተካሄዱ ሲሆን፥ በሁለት የተለያዩ መድረኮች ነው የተካሄደው።

በመጀመሪያው መድረክም የኢትዮ-አውስትራሊያ-ኒውዚላንድ የቢዝነስ ፎረም የተካሄደ ሲሆን፥ በፎረሙ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቶች የሚያሰፉ ውይይቶች ተደርገዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆነች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆነች

ህዳር 15/03/2010

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች።

ሀገሪቱን ለሁለት ዓመት ለሚቆየው ለዚሁ ሹመት ያበቃት በዘርፉ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ያስመዘገበችው ውጤት ነው ተብሏል።

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የሊቀ መንበርነት ቦታውን ከማሊ በመቀበል ሥራዋን እንደምትጀምር ነው የተገለፀው።

ከእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ተጠቃሚ ለመሆን ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል - ፕሬዚዳንት ሙላቱ

 ከእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ተጠቃሚ ለመሆን ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ ይገባል - ፕሬዚዳንት ሙላቱ

ህዳር 11/03/2010

ሀገሪቱ ካላት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ተጠቃሚ እንድትሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጠንካራ ትብብር በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ።

ዛሬ የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር በዘርፉ ላይ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሞዴል ተዋናዮች ሽልማት እና እውቅና ሰጥቷል።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ከኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ክርስቲ ካሊጁሌድ ጋር ተወያዩ

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ከኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ክርስቲ ካሊጁሌድ ጋር ተወያዩ

ህዳር 7/03/2010

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ክርስቲ ካሊጁሌድን በብሔራዊ ቤተ መንግስት ተቀብለው አነጋገሩ።

ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች የኢትዮጵያ እና የኢስቶኒያን ሁለንተናዊ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፥ ኢትዮጵያ ከሁሉም የአውሮፓ ሀገራት ጋር በተለይም ባልቲክ ስቴት ከሚባሉት ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው

 ኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው

ህዳር 6/03/2010

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አራት ቦይንግ 777 ለመግዛት ተስማማ።

አየር መንገዱ የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ሲሆን፥ መቀመጫውን ቺካጎ ካደረገው የቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ቦይንግ 777 ኤከስን ለመግዛት እየተነጋገረ ይገኛል።

ስምምነት ከተደረሰባቸው አራት አውሮፕላኖች መካከል ሁለቱ፥ ባለፈው ሰኔ ወር በፓሪስ በተደረገው የአየር ትራንስፖርት አውደ ርዕይ ስምምነት የተደረገባቸው መሆኑ ተነግሯል።

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper