በቻይና ኩባንያዎች የተገነቡ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በቀጣዩ ወር ይመረቃሉ

ሰኔ 12 ,2009

በቻይና ኩባንያዎች የተገነቡ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሚቀጥለው ወር እንደሚመረቁ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፐሬሽን አስታወቀ፡፡ 

በሚቀጥለው ወር የሚመረቁት ሁለቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ፥የመቀሌ እና የኮቦልቻ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ናቸው፡፡

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቻይና ኮሙኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ኩባንያ(CCCC) ሲሆን፥የኮቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ደግሞ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን (CCECC) መገንባታቸውን ኮርፕሬሽኑ ገልጿል፡፡

 

"አምራች ዜጋን ለማፍራት የቤት ጥያቄን መመለስ ተገቢ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

መጋቢት  04/2009

 

"የአገሪቱን ልማት የሚያፋጥን አምራች ዜጋ ለማፍራት የቤት ጥያቄን ለመመለስ መስራት አለብን" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ።

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦሌ አራብሳና በቦሌ አያት ሶስት፣ አራት እና አምስት ሳይቶች ግንባታቸው የተጠናቀቁ የ20/80 የቤት ፕሮግራሞችን በስፍራው ተገኝተው መርቀዋል።

 በሳይቶቹ የተመረቁ ቤቶች ለልማት ተነሺዎች የተላለፉ የቦሌ አያት ሶስት፣ አራትና አምስት 1ሺህ 811 እንዲሁም በቦሌ አራብሳ ሳይት 20 ሺህ 100 ቤቶች ናቸው።

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት የተለያዩ ፖሊሲዎችን በመንደፍ ዘላቂነት ያለው ልማት አረጋግጦ፣ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው።

 በዚህ ሂደት በከተሞች የሚንጸባረቁ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች መነሻ የሆነው ድህነትን ለመግታት ያልተቋረጠ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያና ሕንድ የንግድና ኢንቨስትመትንት ግንኙነታቸው ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገለጹ 

ጥር 29/2009 ዓ.ም

ኢትዮጵያና ሕንድ በንግድና ኢንቨስትመትንት ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገለጹ።

 የኢትዮ-ሕንድ የንግድ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮጵያና ሕንድ በኢኮኖሚው ዘርፍ ስትራቴጂያዊ ትብብር ያላቸው አገራት ናቸው።

 ኢትዮጵያም የሁለቱ አገራትን የጋራ ተጠቃሚነትና ፍላጎት በሚያስጠበቁ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሳተፍ ያላትን ትብብር ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

 የሕንድ ባለኃብቶች በኢትዮጵያ በግብርናና በአምራች ዘርፍ በስፋት ተሰማርተው እንደሚገኙ ሚኒስትር ዴታዋ አስረድተዋል።

ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ ጅቡቲ ያለው የባቡር ፕሮጀክት ተመረቀ

ታህሳስ 04/2009 ዓ.ም

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለሁለቱ አገራት ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።

 ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ ጅቡቲ ያለው የ 100 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ መስመሩን መርቀው ከፍተውታል።

 የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር 758 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ ርዝመት ሲኖረው በኢትዮጵያ በኩል መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።

 

ኢጣሊያ ለኢትዮጵያ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ምርት ማሻሻያ የ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ህዳር 15/2009 ዓ.ም

ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ቆዳና የቆዳ ውጤቶችን ምርት ለማሻሻል የሚውል የ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ልታደርግ ነው።

የድጋፍ ስምምነቱ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣በተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) እና በኢትዮጵያ የኢጣሊያ አምባሳደር ጆሲፔ ሚስትሬታ መካከል ዛሬ ተፈርሟል።

ድጋፉ በኢትዮጵያ አነሰተኛና መከካከለኛ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትርን ለማሳደግ የተባበሩት መንግስታት ኢንደስትሪ ልማት ድርጅት ለሚያደርገው ''የቴክኒካል ድጋፍ ፕሮጀክት'' ምዕራፍ ሁለት ማስቀጠያ የሚውል ነው።

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper