ምርታቸውን ለውጭ ገበያ የሚያርቀቡ ኩባንያዎች ወደ ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየገቡ ነው

 

ምርታቸውን ለውጭ ገበያ የሚያርቀቡ ኩባንያዎች ወደ ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየገቡ ነው

ከወራት በፊት በተመረቀው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ኩባንያዎች እየገቡ ነው ።ፓርኩ ከወራት በፊት የተመረቀ ሲሆን፥ በ75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ለግንባታው ከ90 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጭ የተደረገበት ይህ ፓርክ በውስጡ የማምረቻ ሼዶችን ጨምሮ የአገልግሎት ማዕከላትን

አካቶ የያዘ መሆኑ ተነግሯል።የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽንኮሚሽነር አቶ ፍጹም አረጋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የውጭ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ገብተው እንዲያመርቱ ከየኩባንያዎቹ ጋር ስምምነት እየተደረገ ነው።ከመስከረም ወር ጀምሮም የደቡብ ኮሪያ፣ የቻይና፣ የጣሊያንና የአሜሪካ ኩባንያዎች በፓርኩ ውስጥ የማሽን ተከላና ማሽነሪዎችን የማጓጓዝ ሥራ አከናውነዋል ብለዋል ።በአሁኑ ወቅትም ከተገነቡት ሼዶች ውጪ በሚገኝ ባዶ ቦታ ላይ የጣሊያኑ ካርኒፋ በ20 ሄክታር ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሴንቴቲክ አልባሳት ምርቶችን የሚያመርት ፋብሪካ እየገነባ መሆኑ ተነግሯል።በሌላ በኩል ሻንቴክስ እና ፓንኮንክ የተባሉ የቻይና የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች የራሳቸውን ማምረቻ በፓርኩ መገንባት ጀምረዋል ነውየተባለው።ይህ ፓርክ በዋናነት ለጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርት በሚያመች መልኩ የተገነባው ሲሆን፥ ከግንባታው ጀምሮ እስካሁን ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።ሙሉ ለሙሉ ምርት ማምረት ሲጀምርም እስከ 20 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል ሲፈጥር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬም ያስገኛል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።በተጨማሪም ፓርኩ ለአውሮፕላን ማረፊያና እየተገነባ ላለው የባቡር ትራንስፖርት ቅርብ መሆኑ፤ ለኩባንያዎቹ አፈጻጸም ውጤታማነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።በተያያዘ ዜና ቀደም ብሎ ስራ በጀመረው በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ 18 ኩባንያዎች ወደ ምርት በመግባታቸው በተሻለ ሁኔታ ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ መሆኑን ተገልጿል።በፓርኩ በተጀመረው የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ጊዜ ቆጣቢ አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፥ ኩባንያዎችም በቀላሉ የፈለጉት ጉዳይን ለማከናወን እንዲችሉ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ተብሏል።በአሁን ወቅት ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፥ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ ለ60 ሺህ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ነው የታወቀው።

ምንጭ፡-ኤፍቢሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper