የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ከ67 በመቶ በላይ ደርሷል

 

የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 67 በመቶ በላይ ደርሷል

የካቲት22/2010

ከ147 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ከ67 በመቶ በላይ ደርሷል።በ2009 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ ግንባታው የተጀመረው ፓርኩ፤ በ102 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በፓርኩ ባደረገው ቅኝትም፥ የፓርኩየሼዶች ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ተመልክቷል።የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኤፍሬም በቀለ፥ የሼዶቹ ግንበታ አፈፃፀም 86 ከመቶ በላይ መድረሱን እና የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ የቀሩ መሆናቸውን

ተናግረዋል።ፓርኩ ሲጠናቀቅ በተለያየ ዘርፍ ለሚሰማሩ ኩባንያዎች የሚያገለግሉ 19 የመስሪያ ሼዶች ወይም የመስሪያ ቦታዎችን የያዘ ነው።ከእነዚሀ ሼዶች ውስጥም ስድስቱ 11 ሺህ ካሬ ሜትር፣ ዘጠኙ 5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር፣ አራቱ ደግሞ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ ናቸው ብለዋል አቶ ኤፍሬም።ከፓርኩ አጠገብም 122 ሄክታር መሬት ላይ በፓርኩ ውስጥ ስራ ለሚጀምሩ ባለሀብቶች የማሽን መገጣጠሚያ ማእከል ግንባታም ተጀምሯል።የፓርኩ የውስጥ ለውስጥ እና ወደ ፓርኩ የሚወስደው የመንገድ ስራም ተጠናቆ የመብራት ምሰሶዎች ተተክለዋል።በፓርኩ ውስጥ የሚገነባው የኤሌክትሪክ ሃይል ማጠራቀሚያ ጣቢያ እስከሚጠናቀቅም ከአዋሽ ኤሌክትሪክ ለማስገባት የገመድ ዝርጋታ ስራ እየተከናወነ ነው።የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ የቀሩት ይህ የኢንደስትሪ ፓርክም፤ በዚህ ዓመት ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት አቶ ኤፍሬም።ፓርኩ የማጠናቀቂያ ስራዎችን ጨምሮ አሁን ላይ አጠቃላይ አፈፃፀሙ 67 ከመቶ በላይ መድረሱንም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኤፍሬም በቀለ ተናግረዋል።ኢንዱስትሪ ፓርክ ፓርክ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ መቃረቡን ተከትሎም የአውሮፓ፣ አሜሪካ እና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ቀልብ ስቧል ያሉት አቶ ኤፍሬም፥ እስካሁን ከ20 የሚበልጡ የተለያዩ ሀገራት ባለሀብቶች ፓርኩን መጎብኘታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፡-ኤፍቢሲ

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper