አለም አቀፉ የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ኢንዱስትሪ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

 

አለም አቀፉ የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ኢንዱስትሪ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

የካቲት21/2010

ሁለተኛው አለም አቀፍ የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ኢንዱስትሪ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።ጉባኤው በኢትዮጵያ መንግስትና በመንግስታቱ ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት አዘጋጅነት የሚካሄድ ነው።ትኩረቱን በምግብ ማቀነባበር፣ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶችና በምርት እሸጋና በታዳሽ ሃይል በተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል።

በጉባኤው የሃገር ውስጥና አለም አቀፍ ተቋማት፣ ባለሃብቶች፣ ኩባንያዎች፣ የገንዘብ ተቋማትና በግሉ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ተሳታፊ ይሆናሉ።

ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱ ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ነው የተባለው።

ፈጣን ኢኮኖሚዋ እድገት እያስመዘገበች ያለችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ ተመራጭ የኢንዱስትሪ መዳረሻ መሆኗን ከአግሮ አፍሪካ ድረ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper