ባለፉት ስድስት ወራት 72 ታላላቅ ኩባንያዎች የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት አድርገዋል

 

ባለፉት ስድስት ወራት 72 ታላላቅ ኩባንያዎች የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት አድርገዋል

የካቲት22/2010

 ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 72 ታላላቅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።በዚህም በግብርና ኢንቨስትመንት 5 ኩባንያዎች፣ በግብርና ማቀነባበሪያ 7፣ በማምረቻው ዘርፍ 10፣ በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ 7 እንዲሁም በሃይልና ኢነርጂ ማመንጫ 11 ኩባንያዎች ቅድመ ጉብኝት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ተናግረዋል።

ትላልቅ ኩባንያዎችን ከመሳብ አኳያ የታየው አፈጻጸም ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ቃል አቀባዩ፥ ኩባንያዎቹ ከ5 መቶ ሚሊየን እስከ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አቅም ያላቸው ናቸው ብለዋል።አነስተኛ እና መካከለኛ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ በማድረጉ እንቅስቃሴም፥ 537 ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት የአዋጭነት ጥናት እንዲያካሂዱ ተደርጓል ነው ያሉት።ከዚህ ባለፈም ከእስያና ኦሽኒያ 99፣ ከአውሮፓ 23፣ ከመካከለኛው ምስራቅ 12፣ ከአፍሪካ 13፣ ከሰሜን አሜሪካ ደግሞ 12 ኩባንያዎች ፈቃድ አውጥተው ወደ ስራ መግባታቸውንም ተናግረዋል።ከዚህ ውስጥም በግንባታ 17፣ በማምረቻ 65፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት 2፣ በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች 3 ኩባንያዎች እንደሚገኙበትም ጠቅሰዋል።የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ከመሳብ፣ ለምርቶች ገበያ ከማፈላለግ፣ ከጎብኝዎች ቁጥር አንጻር፣ በቴክኖሎጅ ሽግግርና በቴክኒክና ሙያ ድጋፍ ረገድ ስኬታማ ውጤት መገኘቱንም በመግለጫቸው አንስተዋል።ቃል አቀባዩ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለማድረግም ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።አቶ መለስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫም አዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉ ኤምባሲዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የሰጡት አስተያየት ተፅዕኖ እንደማይፈጥር አንስተዋል።ከአለም አቀፍ ህግ አንጻር ሲታይም የአስቸጓይ ጊዜ አዋጅ አንድ ሉዓላዊ ሃገር በራሷ እንደምትወስን ጠቅሰው፥ የአዋጁ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን እንጂ የውጭ ሃይሎች አለመሆኑን አስረድተዋል።

ምንጭ፡-ኤፍቢሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper