5ኛው ሀገር አቀፍ የኅብረት ሥራ ኤግዚብሽንና ባዛር በስኬት ተጠናቀቀ

5ኛው ሀገር  አቀፍ  የኅብረት  ሥራ  ኤግዚብሽንና  ባዛር  በስኬት  ተጠናቀቀ                                                                               የካቲት7/2010

በኤግዚብሽን መዓከል ከየካቲት 2፣ 2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ እለት የካቲት 7፣2007 ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ሀገር አቀፍ የኅብረት ሥራ ኤግዚብሽንና ባዛር በስኬት ተጠናቋል፡፡በፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና በዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት “የኅብረት ሥራ ማህበራት ግብይት ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው ኤግዚብሽንና ባዛር 291 የሚደርሱ የኅብረት ሥራ ማህበራት አሳትፏል፡፡

በዝግጅቱም ማህበራቱ የተለያዩ ምርታቸውን ይዘው በመቅርብ እራሳቸውን ማስተዋወቅ እና ቀጣይ የገበያ ትስስር መፍጠር ችለዋል፡፡ በተመሳሳይም ወደ 10,000 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጎብኝተውታል ተብሎ የሚታሰበው ዝግጅት ነዋሪውን ጥራት ያላቸው ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡በአሁን ሰዓት በሀገራችን 82 ሺህ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ 381 የኅብረት ሥራ ዩኒዬኖች እና 3 ክልላዊ የኅብረት ሥራ ፌዴሬሽኖች ሲኖሩ በስራቸውም 17 ሚሊዮን የሚደርሱ አባላት አቅፈው ይዘዋል፡፡ እነዚህም ተቋማት 19.9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማካበት የቻሉ ሲሆን፣ 13.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ተቀማጭ አድርገዋል፡፡እነዚህ ማህበራት ሀገሪቷ የተየያዘችውን የኢኮኖሚያዊ እድገት ከማስቀጠል አንጻር እና ሕብረተሰቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚ ከማድረግ እና ጤናማና ፍትሃዊ የገበያ ስርዓት ከመገንባት አንጻር ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ አንዳላቸው በዝግጅቱ ወቅት ተነግሯል፡፡

አርታኢ፡-ሥነፀሀይ

 

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper