መንግስት ለህብረት ስራ ማህበራት መጠናከር ልዩ ትኩረት ይሰጣል-ፕሬዚዳንት ሙላቱ

 

መንግስት ለህብረት ስራ ማህበራት መጠናከር ልዩ ትኩረት ይሰጣል-ፕሬዚዳንት ሙላቱ                     የካቲት2/2010

መንግስት ለህብረት ስራ ማህበራት መጠናከር ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ገለጹ።ፕሬዚዳንቱ 5ኛውን ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ከፍተዋል።በሀገሪቱ እየተመዘገበ ላለው ፈጣን እድገት የህብረት ስራ ማህበራት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቱ ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።በተለይም ለእርሻና መካናይዜሽን የተበጣጠሰ እርሻን በዘመናዊ መልኩ ለማሻሻል እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ግብአት በመመገብ የማይተካ ሚና ነበራቸው።

የህብረት ስራ ማህበራት አባላትን እንዲሁም አርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ በማድረግ፣ የስራ እድል በመፍጠር፣ ከተማና ገጠሩን አስተሳስሮ አምራችና ሸማቹን በግብይት በማስተሳሰር ረገድ እየተጫወቱ ያለውን ፋይዳ ማጠናከር ያስፈልጋልም ብለዋል።ሀገሪቱ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር የህብረት ስራ ማህበራቱ ቁልፍ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል።መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ለመገንባት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ገልጸው የህብረት ስራ ማህበራቱ በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ እንዲታቀፉ ጥሪ አቅርበዋል።መንግስት በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ የሚያደርጉትን ተሳትፎ በልዩ ትኩረት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።የግብርና ምርቶችን በብዛት በጥራት ከማቅረብ በተጨማሪ ወደ አለም ገበያ በመግባት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን እንዲያጎለብቱ የውጭ ገቢ ምርትን የመተካት ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።የእርሻና ተፈጥሮ ኃብት ሚኒስትሩ ዶክተር እያሱ አብርሃ በበኩላቸው፥ የህብረት ስራ ማህበራቱ ዘላቂ የግብይት ትሰስር በመፍጠር ገበያ የማረጋጋት፣ ገጠርና ከተማውን በማስተሳሰር ዘመናዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የጀመሩትን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።የፌደራል ህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፤ ማህበራት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ጤናማ ግብይት በመፍጠር፣ ኢንቨስትመንትና ቁጠባን በማሳደግ፣ የውጭ ገቢ ምርቶችን በመተካትና በሌሎች መስኮች ዘርፈ ብዙ ሚና ተጫውተዋል።በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ17 ሚሊየን በላይ አባላት ያሏቸው 381 የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች እና ከ82 ሺህ በላይ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት እንዳሉ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።በተጨማሪም እነዚሁ ተቋማት ከ13 ቢሊየን ብር በላይ የቆጠቡ ሲሆን፥ ለ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ፈጥረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper