የኢትዮጵያ የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በጃፓን እየተካሄደ ነው

 

የኢትዮጵያ የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በጃፓን እየተካሄደ ነው                                                  ጥር29/2010

የኢትዮጵያ የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በጃፓን ኮቤ እና ናጎያ ከተሞች መካሄድ ጀምሯል።በዛሬው እለት የተጀመረው የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረሙ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑም ተነግሯል።በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል የተመራ የኢትዮጵያ የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ልኡካን ቡድንም በፎረሙ ላይ እየተካፈለ ይገኛል።ልኡካን ቡድኑ ከፎረሙ አስቀድመው በትናንትናው እለት በጃፓን ኦሳካ የሚገኘውን ሮህቶ ፋርማቲኳል ኩባንያን መጎብኘታቸውም ተገልጿል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተሬት ጀነራል፣ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተወጣጡ ልኡካንም ከኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ኩኒዮ ያማዳና ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሌክህ ጁኔጃ ጋር ተወያይተዋል።ልኡካን ቡድኑ ከኩባንያው አመራሮች ጋር በነበራቸው ቆይታም በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት እድሎች እና አማራጮች ዙሪያ በስፋት መክረዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል በዚሁ ወቅት፥ በኢትዮጵያ ሰፊ ቁጥር ያለው አምራች ሀይል በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሩን አብራርተዋል።

እንዲሁም በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ መረጋጋት ኢትዮጵያን በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዳደረጋት መግለፃቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት የንግድና ኢንቨስትመንት አውደ ርዕይ በኩዌት መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የ25 የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች የተሳተፉበት የንግድና ኢንቨስትመንት አውደ ርዕዩ ላይ ኤምባሲዎቸ የየራሳቸውን የማሳያ ቦታ በመውሰድ የየሀገራቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን አሳይተዋል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper