አሜሪካ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ከአደጋ ለመጠበቅና ለመጠገን የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች - አምባሳደር ማይክል ሬነር

 

አሜሪካ  የኢትዮጵያ  ቅርሶችን  ከአደጋ  ለመጠበቅና  ለመጠገን  የሚደረገውን  ጥረት  ትደግፋለች - አምባሳደር ማይክልሬነር                                                                                                                                                         

ጥር29/2010

አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚገኙ ቅርሶችን ከአደጋ ለመጠበቅና ለመጠገን የሚደረገውን ጥረት መደገፏን እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬነር ገለፁ።ሀገሪቱ በ“አሜሪካ አምባሳደርስ ፈንድ” በኩል ላሊበላ ቤተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጥገና ድጋፍ ማድረጓን ያስታወሱት አምባሳደሩ፥ በቀጣይ ለሚደረጉ ጥገናዎችም ሀገሪቱ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ተናግረዋል።የላሊበላ ቤተ ጎለጎታ ቤተ ሚካኤል ቤተ መቅደሶች ጥገና ስራን ለማከናወን የአለም ሞኑመንት ፈንድ እና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከትናንት በስቲያ በላሊበላ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ከስምምነቱ በኋላ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬነር፥ ላሊበላ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያገናኘ መንፈሳዊ ድልድይ ነው ይላሉ።ከቀጣዩ የካቲት ወር ጀምሮ ለሚካሄደው የላሊበላ ቤተ ጎለጎታ ቤተ ሚካኤል ቤተመቅደሶች ጥገና ፕሮጀክትም የአሜሪካ አምባሳደርስ ፈንድ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በፀሀይና ዝናብ መፈራረቅ እና ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ለተለያዩ ጉዳቶች ሲዳረጉ ይታያል።

ከአፄ ሀይለስለሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የጥገና ስራዎች የተከናወኑ ቢሆንም ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ያየለበት ሁኔታ የሚታይባቸው ሁኔታዎች ተከስተዋል።

የቤተ አማኑኤል እና ቤተ መድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያናትን በሲሚንቶ ለመጠገን የተደረገው ሙከራም ለዚሁ አንዱ ማሳያ ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም፥ ይህን ችግር ለመፍታት የውጭ እና የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ያሳተፈ ጥናት በማድረግ አስቸኳይ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ቤተ ክርስቲያናት ተለይተዋል ይላሉ።

ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑና ከሁሉም ቀድሞ ጥገና ያስፈልገዋል የተባለው የቤተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከሶስት አመት በፊት ተጠግኗል።

ጥገናው ስኬታማ በመሆኑም ከዚህ የተገኘውን ልምድ በመቀመር የቤተ ጎለጎታ ቤተ ሚካኤል ቤተመቅደሶችን ለመጠገን ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ።

በቤተ ጎለጎታ ወሚካኤል ያለው ስንጥቅ በህንፃው ውስጥ ውሃ እንዲገባ አድርጓል ያሉት ዶክተር ሂሩት፥ ከውጭ የሚታየው የቅርሱ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ ገፅታውም በኤክስሬይ ታይቶ ችግሮቹ መለየታቸውን አብራርተዋል።

ጥገናውን ለማካሄድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ እና በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም በአለም ሞኑመንት ፈንድ ጥናት የተደረገ ሲሆን፥ ቤተ መቅደሶቹ ከተሰሩበት ተፈጥሯዊ አለት ጋር በሚመሳሰል ግብአት ይጠገናሉ ነው ያሉት።

በላሊበላ እንደ ቤተ ማርያም፣ ቤተ መድሃኒያለም እና ቤተ አማኑኤል ያሉ አምስት ቤተክርስቲያኖች በዝናብ እና ፀሃይ መፈራረቅ ከፍተኛ ችግር ሲደርስባቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2009 አራት መጠለያዎች ወይንም ሼዶች ተተክሎላቸዋል።

እነዚህ መጠለያዎች ግን በተቀመጠላቸው ጊዜ አለመነሳታቸው ለቅርሶቹ የስጋት ደውል ማሰማት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት፥ መጠለያዎቹ መነሳታቸው አይቀሬ ነው፤ ጥገናው ግን ይቀደማል ይላሉ።

የዩኔስኮ ባለሙያዎችም በቅርቡ መጠለያዎቹ በቅርሶቹ ደህንነት ላይ የሚኖራቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ ተመልክተዋል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

የቤተ ክርስቲያናቱ ጥገና ተደርጎ ሲጠናቀቅ አልያም ጥገናው እየተካሄደ ጎን ለጎን በሳይንሳዊ መንገድ ይነሳሉም ብለዋል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper