30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ነው

 

30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ነው                                                        ጥር21/2010

30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባዔ “ዘላቂ የፀረ-ሙስና ዘመቻ ለአፍሪካ ስር ነቀል ለውጥ” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ መሃመት ሊቀ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግርም፥ የአፍሪካ ሀብረት ማሻያ በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

እንዲሁም በፀረ ሙስና የሚደረገውን ዘመቻ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል አለበት ያሉት ሊቀ መንበሩ፥ የነፃ ንግድ ቀጣና እና የአፍሪካን አየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ ማድርግ የሚሉት ላይ የሚሰሩ ስራዎች እንዲጠናከሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ደቡብ ሱዳንን በተመለከተም፥ በሀገሪቱ ያለው የሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀው፤ በተለያየ ጊዜ የሚፈረሙ የሰላም ስምምነቶችን የሚጥሱ ወገኖች ላይ ማእቀብ የሚጣልበት ጊዜ ደርሷል ብለዋል።

በደቡብ ሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት በህዝቡ ላይ እያስከተለ ያለውን ችግር ከዚህ በኋላ አንታገስም ሲሉም ተደምጠዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ሁቴሬስ በበኩላቸው፥ የመንግስታቱ ድርጅ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ከስደተኞች ጉዳይ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በስደተኞች አቀባበል እና አያያዝ ዙሪያም አፍሪካ ለበርካታ የዓለም ሀገራት ትምህjርት የምትሰጥ ናት ብለዋል።

በጉባዔው ላይ የተገኙት የአረብ ሊግ ዋና ፀሃፊ አህመድ አቦውል ጊሀት፥ የአፍሪካ- አረብ ግንኙነት የሚጠናከርበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከስደት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመከላከል በሚሰራው ስራ ላይም የአረብ ሊግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉቤዔው ፀረ ሙስና ዘመቻ፣ የአፍሪካ ህብረት ማሻሻያ፣ የነፃ ንግድ ቀጣና እና የአፍርካን አየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ ማድርግ የሚሉት ዋና መነጋገሪያ ይሆናሉ ተብሎ ከሚጠበቁት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

በዚህም የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በዚህ ስብሰባ ነፃ የንግድ ቀጣና፣ የአፍሪካን አየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ እንዲሆን እንዲሁም ነፃ የሰዎች እና የሸቀጥ ዝውውር ላይ ውሳኔ ያሳልፏሉ ተብሉ ይጠበቃል።

ከእነዚህ ነጥቦች ባለፈም መሪዎቹ በአህጉሪቷ የደህንነት እና ፀጥታ ስጋቶች ዙርያ፣ በፀረ ሽብር ዘመቻው ላይ በተወሰኑ ሀገራት የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማስቆም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ከጉባኤው ይጠበቃሉ።

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper