ኢትዮጵያና ኖርዌይ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ኖርዌይ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት ተስማሙ

ጥር18/2010

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት ከስምምነትደርሰዋል።የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኖርዌይ አቻቸው ኤሪክሰን ሶሪይዴን ዛሬ በፅህፈት   ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይትም፥ ኢትዮጵያና ኖርዌይ በጋራ ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን የትብብር መስኮች ለመለየት ተስማምተዋል።ዶክተር ወርቅነህ፥ ኢትዮጵያ

በትምህርት እና በአረንጓዴ ልማት ዘርፎች ከኖርዌይ ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገልፀዋል።ሚኒስትሩ ኖርዌይ እውነተኛ የኢትዮጵያ የልማት አጋር ናት ሲሉም ተናግረዋል።የኖርዌዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሪክሰን ሶሪይዴ በበኩላቸው፥ ሃገራቸው ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ ገልፀዋል።ሚኒስትሮቹ ኖርዌይ እና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና መረጋጋት አብረው እንደሚሰሩ መነጋገራቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper