የመጀመሪያው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በአዲስ አበባ ከተማ ሊገነባ ነው

 

የመጀመሪያው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ  ማጠራቀሚያ በአዲስ አበባ ከተማ ሊገነባ ነው

ታህሳስ 28/04/2010

   ለአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጣቢያ በቂርቆስ ክ/ከተማ ሊገነባ በጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አማካኝነት የመሰረተ ድንጋይ ታህሳስ 28፣ 2010 ዓ.ም ተጣለ፡፡ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያው 500 ካሬ ሜትር ስፋት መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን  ከከተማው ነዎሪ ቤት እና ከተቋሟት ተሰብስቦ የሚወጣው ቆሻሻ የሚለይበት እና ወደ ዋና የቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ ወይም የዑደት ፋብሪካ እስኪ ጓጓዝ የሚቆይበት ነው፡፡

በአሁን ወቅት ያሉት የቆሻሻ መቆያ ስፍራዎች በአግባቡ ያልተከለሉ እና በአነስተኛ ስፍራ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት አካባቢን መጥፎ ጠረን እና የተበላሸ ገጽታ እያላበሱ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዘመናዊ እና በተሟላ ሁኔታ ስላልተገነቡ ከቁሻሻዎች የሚወጣው ፈሳሽ ከአፈር ተንጠባጥቦ በመቀላቀል እና በመቡነን ለህብረተሰቡ የጤና እክል ይፈጥር ነበር እንደ አቶ ማስረሻ አስናቀው፣ የአዲስ አበባ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ አገላለጽ፡፡ አሁን ሊገነባ የታቀደው ዘመናው ጣቢያ ግን ይህን ፈሳሽ ከአፈር ጋር ሳይቀላቀል የሚያጠራቅምበት እና የሚያስወግድበት አሰራር ተያይዞ ስለሚገነባለት ከዚህ የጤና ችግር ይገላግለናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡም የተለያየ እንድ ጽዳት ሰራተኞች ቢሮ፣ ማረፊያ፣ መተጣጠቢያ እና የተከለለ አረንጓዴ ስፍራ መገልገያዎች ይኖሩታል፡፡

እንደነዚህ ያሉ ተጨማሪ 84 ጣቢያዎች በቀጣዩ ሦስት ወር ውስጥ በአስሩም ክፍለ ከተማዎች እንደሚገነቡም ታውቋል፡፡

የመሰረተ ድንጋይ የማኖሩ ስነ-ሥርዓት የተከናወነው በሁለተኛው ዙር የአካባቢ ማፅዳት ንቅናቄ ላይ የከተማው ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣ የከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀይሌ ፍሰሃ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ነበር፡፡ በዝግጅቱም ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያምን ጨምሮ አካባቢውን በማጽዳት እና ችግኝ በመትከል ተሳትፈዋል፡፡ ይህ ከተማ አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ “እኔ አካባቢይን አጸዳሁ! እናንተስ?” በሚል መፈክር ዓመቱን ሙሉ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

 ምንጭ፡- ስነ-ፀሀይ አሰፋ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper