የኢትዮጵያና የኳታር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የተጀመረው የጋራ ጥረት እንደሚቀጥል ተገለፀ

 

የኢትዮጵያና የኳታር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የተጀመረው የጋራ ጥረት እንደሚቀጥል ተገለፀ

ታህሳስ 21/04/2010

 የኢትዮጵያና የኳታር የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የተጀመረው የጋራ ጥረት እንደሚቀጥል ተገለፀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኤታማጆር ሹም ጀነራል ጋኒም ሻሂን አል ጋኒም የሚመራ የኳታር ልዑካን ቡድንን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያና ሕዝብ ግንኙት ዴሊቨሪ ዩኒት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ፥ የኢትዮጵያና የኳታር ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣ በመሆኑ በመሪዎች ደረጃ የስራ ጉብኝት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚሁ መሰረት ባለፈው ዓመት የኳታሩ ኢሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ በኢትዮጵያ፤ በዚህ ዓመት ደግሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኳታርን መጎብኝታቸው የሚታወስ ነው።

አቶ ዛዲግ እንደገለጹት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኳታር መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራና በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በውይይቱ ኳታርና ኢትዮጵያ በቀጠናው እና በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሰላምና መረጋጋት በሚሰፍንበት ጉዳይ ላይ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ነው አቶ ዛዲቅ የገለጹት።

በተጨማሪም ሁሉቱ አገራት ከመከላከያ ውጭ ባሉ ተግባራት ላይ በጋራ ለመስራት ከዚህ በፊት ያደረጉትን ስምምነት ይበልጥ ለማሳደግና ለማፋጠን በሚችሉበት መስክ ላይ መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

ኳታር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የገባችውን ቃል ይበልጥ እንድታፋጥንም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

ኳታርም በኢትዮጵያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ኤታማጆር ሹሙ ጀነራል ጋኒም ሻሂን አል_ጋኒም መግለጻቸውን አቶ ዛዲቅ ተናግረዋል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper