የጃፓኑ አልባሳት አምራች ዩኒቅሎ በኢትዮጵያ ፋብሪካውን ከፈተ

 

የጃፓኑ አልባሳት አምራች ዩኒቅሎ በኢትዮጵያ ፋብሪካውን ከፈተ

ታህሳስ 19/04/2010

 የጃፓኑ አልባሳት አምራች ኩባንያ ዩኒቅሎ በአፍሪካ የመጀመሪያውን አልባሳት ማምረቻ በኢትዮጵያ መክፈቱን አስታወቀ። አልባሳት ማምረቻ ፋብሪካው የሙከራ ምርቱን በቅርብ ጊዜ ይጀምራል ተብሏል። ፋብሪካው ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብም ከፋብሪካው ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል። የፋብሪካው ምርቶች በዋናነት ለአሜሪካና አውሮፓ ገበያዎች ይቀርባሉም ነው የተባለው።

በኢትዮጵያ ያለው ርካሽ የሰራተኛ ጉልበትና በአሜሪካ ገበያዎች ለኢትዮጵያ ምርቶች የሚሰጠው ማበረታቻም ፋብሪካውን በኢትዮጵያ ለመትከል እንዳበቃውም ፋብሪካ ገልጿል። ከዚህ ባለፈም ከሌሎች ሃገራት በተሻለ ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ገበያዎች ቅርብ መሆኗ ተመራጭ እንዳደረጋትም ጠቅሷል። አለም አቀፉ የጃፓን ኩባንያ ሹራብ፣ ሸሚዝ፣ ቲሸርት ሱሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ አልባሳትን ዲዛይን በማድረግ፣ በማምረትና በማዘጋጀት ይታወቃል።

ምርቶቹንም በዋናነት በእስያ፣ በአሜሪካና አውሮፓ ገበያዎች በመላክ ትርፋማ መሆኑም ይነገራል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper