የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተወያዩ

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተወያዩ

 ታህሳስ 18/04/2010

 

   የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተወያዩ። ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ነው ዛሬ በአዲስ አበባ ተገናኝተው የመከሩት። በኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ በሰው ሀይል አቅም ግንባታ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያም ተወያይተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያም የመከሩ ሲሆን፥ ግድቡን በተመለከተ በመርህ ደረጃ በተደረሰው ስምምነት መሰረት እንሰራለን ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ውይይት የሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን ራሱን ችሎ በሶስትዮሽ (ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን) ደረጃ የሚካሄድ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ በግብፅ ላይ የጎላ ተፅእኖ እንደማይኖረው ሀገሪቱ በተደጋጋሚ ስትገልፀው የነበረው አቋም ዛሬም ተመሳሳይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይህ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ዛሬ የተደረገው ውይይት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅሞች ሊያጠናክሩ በሚችሉ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረው አቅጣጫ የሚሰጡበት እና በየሁለት ወሩ የሚካሄድ ነው።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper