የወጋገን ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ተመረቀ

 

የወጋገን ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ተመረቀ

መስከረም 22/2010

በ805 ሚሊዮን ብር የተገነባው የወጋገን ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ  መስከረም 20፣ 2010 ዓ.ም ተመረቀ፡፡ የምርቃት ሥነ- ስርዓቱ  ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ እንዲሁም የባንኩ ባለስልጣናት፣ የአክሲዎን ባለቤቶች እና የተለያዩ የባንኩ ዘርፍ ባለሙያዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ከዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ተካሄዷል፡፡

የህንፃው ግንባታ ወደ አምስት ዓመታት የፈጀ ሲሆን የግንባታ ስራውም የተከናወነው በቻይና ጂዓንዚ ኮርፖሬሽን ፎር ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ኤንድ ቴክኒካል ኮኦፖሬሽን ነው፡፡ በስነ-ህንፃ እና በመዋቅር ዲዛይኑ ሁለት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች፣ ኢቲጂ ዲዛይነር እና ኮንሰልታሲ እና ኤምኤች ኢንጂነሪግ እንደ የደረጃው ተሳትፈዋል፡፡

107 ሜትር የሚረዝመው ህንፃው በአጠቃላይ 33 ወለሎች አሉት፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ህንፃው በቂ የፓርኪንግ ቦታ ያቀፈ ሲሆን ባንኩ ለኪራይ የሚያወጣውን ወጪ አስቀርቶ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

ወጋገን ባንክ በ1981 ዓመተ ምህረት በአስራ ስድስት ባለዕራዪ ግለሰቦች የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአክሲዎን ባለቤቶች ቁጥሩን ከ3000 በላይ አድርሷል፡፡ የባንኩ የተከፈለ ካፒታልም 2 ቢሊዮን ብር ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡

 አርታኢ፡ ስነ ፀሃይ አሰፋ

 

 

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper