ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በተመድ 72ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብተዋል

 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በተመድ 72ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብተዋል

መስከረም 8/ 2010

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 72ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በትናንትናው እለት ወደ ኒውዮርክ አቅንተዋል።

በትናንትናው እለት ወደ ኒውዮርክ ያቀናው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተመራው ልኩም ዛሬ ኒውዮርክ ገብቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 72ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፥ ከጉባኤው ባሻገር የጎንዮሽ ስብሰባዎችን አንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የአየር ንብረት ለውጥ፣ አካባቢያዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ እና የዘላቂ ልማት ግቦች ዋና የመወያያ ርዕሶች ይሆናሉ።

በጉባኤው በሰላም ማስከበር ዙሪያ ምክክር የሚደረግ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የወሩ ፕሬዝዳንት እንደመሆኗ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይመሩታል።

በዚህ ስብሰባ በሰላም ማስከበር ተሳትፎ ያላቸውና ሰላም አስከባሪ ሃይል ያዋጡ ሀገራት በመሪዎቻቸው ደረጃ የሚሳተፉ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper