ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመሰማራት ውል አስረዋል

 

1 ቢሊየን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመሰማራት ውል አስረዋል

ጳጉሜ 04/2009

በፈረንጆቹ 2016/17 1 ነጥብ 48 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ካፒታል ያስመዘገቡ የተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመሰማራት ውል ማሰራቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ።

ሺንዋ የዜና ምንጭ የኮሚሽኑን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሀይሉን ጠቅሶ እንደዘገበው፥ ሀገሪቱ ባለፈው በጀት አመት በጥቅሉ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስባለች።

ይህም ከቀደመው አመት አንጻር የ20 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት በተመዘገበ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትም ለ71 ሺህ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ዘገባው ጠቁሟል።

ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ

 

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper