ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከቻይና የተለያዩ የኢንዱትሪ ማህበራት ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

 

/ ኃይለማርያም ከቻይና የተለያዩ የኢንዱትሪ ማህበራት ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

ነሐሴ27/2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቻይና ከተለያዩ የኢንዱትሪ ማህበራት የተወጣጣ ልዑካን ቡድን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፥ በኢትዮጵያና ቻይና መንግሥት መካከል የጠበቀ ወዳጅነት መኖሩን ለልኡካን ቡድኑ አብራርተዋል።

ከኢትዮጵያ ሕዝብ 70 በመቶው አምራች ወጣት መሆኑን፣ ህዝብ ሰላም ወዳድ መሆኑን እና መንግሥት ለወጣቱ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ካለው ፍላጎት የተነሳ በርካታ ግል ኢንቨስትመንትን ለማሳተፍ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑም ለልኡካኑ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለገበያ ተደራሽነት ምቹ መሆኗን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፥ የቻይና ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ በስፋት ቢገቡ ውጤታማ ከሚያደሯቸው በርካታ ምቹ ሁኔታዎች ጥቂቶቹ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው፥ የቻይና ኢንቨስተሮች በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በአግሮ ኢንዲስትሪዎችና የምግብ ምርቶች የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ገልጸዋል።

አያይዘውም ቡድኑ በቻይና በሚኒሊየኖች የሚቆጠሩ ኩባንዎች አባል ከሆኑባቸው ማህበራት የተውጣጡ መሆናቸውን ጠቁመው በኢትዮጵያ ውጤታማ ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ወደ አገራቸው ሲመለሱም የታዘቡትን ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ባለሐብቶች እንደሚያካፍሉ ቃል መግባታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈተ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

Log in

Contact us

Wafa Marketing & Promotion PLC

Mexico Biftu Building 8th & 11th Floor ,

In front of Addis Ababa University School Of Commerce

Addis Ababa, Ethiopia

Phone: +(251) 115 525031

JoomShaper